30 ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች በምስራቅ አፍሪካ የስነጾታ እኩልነት ተነሳሽነት መርሃግብርን አስጀመሩ – Women Deliver

30 ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች በምስራቅ አፍሪካ የስነጾታ እኩልነት ተነሳሽነት መርሃግብርን አስጀመሩ

፳፰ ኦክቶበር ፳፻፳፬ l ዊሜን ዴሊቨር (Women Deliver) በምስራቅ አፍሪካ የጾታ እኩልነት የሚያቀነቅኑ ለለውጥ የሚሟገቱ የታዳጊ መሪዎች የመጀመሪያውን ህብረትን የሚመሩ 30 ወጣት አንቂዎችን ዛሬ እያስተዋወቀ ነው። 

ፕሮግራሙ ወጣት ተሟጋቾች የገንዘብ ድጋፍ፣ ግብዓቶችን፣ ስልጠናዎችን እና ውሳኔ ሰጪዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል የሁለት አመት ተነሳሽነት ሲሆን ይህም የተሟጋችነት ጥረታቸውን በአገር አቀፍ፣ በክልላዊ እና በአለም አቀፍ ቦታዎች በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጃገረዶችን የአካል መብት ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው። ዊሜን ዴሊቨር ፕሮግራሙን በሌሎች ክልሎች በየዓመቱ በየተራ ያካሂዳል።

“ወጣትዎች፣ በአንድነት በማሰባሰብ አለም አቀፋዊ አንድነትን በማራመድ የፖሊሲ ለውጥን የሚያስገኝ ጉልበታም የአንድነት ድምጽ መመስረት ይችላሉ፣” ከታንዛኒያ የሆነችው የህብረቱ አባል ክላራ ቤንጃሚን (24) እንዳለችው።

የመጀመሪያው የታዳጊ መሪዎች ፕሮግራም ህብረት እድሜያቸው ከ15 እስከ 29 የሚደርሱ ከቡሩንዲ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ የተውጣጡ ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎችን ያካተተ ነው። የምስራቅ አፍሪካው ህብረት ከኦክቶበር 2024 እስከ ሴፕቴምበር 2026 ይካሄዳል።

“ወጣቶች ፍላጎቶቻቸው እና ምኞቶቻቸው የሚታወቁበት እና የሚተገበሩበት የተሻለ አለም እንዲመጣ የሚሟገቱበትን ምኞታቸውን እና ቁርጠኝነታቸውን የሚያስተላልፉበት ጊዜው አሁን ነው።” የህብረቱ አባል ኤደን አለም (28) ከኢትዮጵያ እንደተናገረችው።

ከ35 አመት በታች የሆኑ 116.8 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ምስራቅ አፍሪካ በውሳኔ አሰጣጥ ስፍራዎች ላይ የወጣቶች ተሳትፎ ሙሉ አቅም ያላት ክልል ነች። ነገር ግን በተለይ በወጣትነት እድሜ ያሉ ልጃገረዶችን፣ ሴቶችን፣ እና የተለያየ የስነጾታ መለያ ያላቸውን ሰዎች በሚነካ መልኩ የጸረ መብቶች ስሜቶች መነሳሳት ምክንያት ወጣት ተኮር እና በወጣቶች ላይ መሰረት ያደረገ የተሟጋችነት ስራ እጅግ ጠቃሚ ይሆናል። በእነዚህ ተግዳሮቶች ላይ የአየር ንብረት ቀውስ ተጨምሮ ከቅርብ አመታት ወዲህ ሚሊዮኖችን የሚጎዱ አደገኛ ድርቆችን እያስከተለ ነው። 

ዊሜን ዴሊቨር በማህበረሰቦቻቸው ውስጥ ይበልጥ እኩልና ዘላቂ የወደፊት ተስፋ ለማስቀጠል የድጋፍ ግባቸውን ማራመድ ስለሚቀጥሉ የታዳጊ መሪዎች ፕሮግራም በአካባቢው ካሉ ወጣቶች ጋር ያላቸውን አጋርነትና አንድነት ለማጠናከር ይረዳል የሚል እምነት አለው።

“አንድ መሆን ጠቃሚ ነው ምክንያቱም የሌሎችን ልጆች እና የወደፊቱን ትውልድ ታሪክ መቀየር እንችላለን።” የህብረት አባል ሚሪያም ሙዋሩ (15) ከኬንያ እንደተናገረችው።

የሚዲያ ጥያቄዎች፦ ኪም ሉፍኪን፣ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር፣ media@womendeliver.org

ስለ ዊሜን ዴሊቨር፦

ዊሜን ዴሊቨር በአንድ ትልም የሚመራ አለም አቀፋዊ የአድቮኬሲ (ተሟጋች) ድርጅት ነው፦ ትልሙም እያንዳንዷ ልጃገረድ እና ሴት ሙሉ የአካል መብትን እና ጤንነትን አስመልክቶ መብቶቿን ትለማመዳለች የሚል ነው። በተጨማሪ www.womendeliver.org ላይ የበለጠ ይወቁ።